ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከአልጀሪያ ፕሬዚዳንት የተላከ መልዕክት ተቀበሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአልጀሪያ ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ቴቡኔ የተላከ መልዕክት መቀበላቸውን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ ዛሬ ጠዋት የአልጀሪያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍን በጽሕፈት ቤታቸው መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡
እንደልዩ መልዕክተኛ ከፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ቴቡኔ የተላከ መልዕክትንም ማድረሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና በአልጀሪያ መካከል ያለውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል።