Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ኤሌክትሮኒክ የተግባቦትና የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ኤሌክትሮኒክ የተግባቦትና የመረጃ ልውውጥ ስርዓት (ኢ-ፒፒዲ) ይፋ ሆኗል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሀኪም ሙሉ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሰብስብ አባፊራ ፈርመውታል።

የስምምነቱ ዋና ዓላማ የግሉን ዘርፍ ይበልጥ በማጠናከር ለኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ነው ተብሏል።

ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየተገናኙ የሚመካከሩበት ኤሌክትሮኒክ ወይም ዲጂታል የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የውይይት፣ የተግባቦትና የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ይፋ ሆኗል።

ዲጂታል ስርዓቱ የግሉ ዘርፍ ስራዎቹን በሚያከናውንበት ወቅት የሚያጋጥሙትን መሰናክሎች ፈጥኖ ለመንግስት በማሳወቅ ፈጣን ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑ መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.