Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ባልተጠናቀቀ ግንባታ ስራ በጀመሩ አልሚዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ባልተጠናቀቀ ግንባታ ስራ በጀመሩ 19 አልሚዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን የክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሀላፊ አቶ ኢስማኤል ዩሱፍ እንደገለፁት ፥ በክልሉ ባልተጠናቀቀ ግንባታ ስራ የጀመሩ አልሚዎች ግንባታ እንዲያጠናቅቁ ተደጋጋሚ የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ሲሰጡ ቆይተዋል።

በተጨማሪም ባልተጠናቀቀ ሕንፃ ላይ ተከራይተው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ድርጅቶች ለህዝብ ደህንነት ሲባል በሦስት ወራት ውስጥ ወደ ተጠናቀቁ ሕንፃዎች እንዲዛውሩም መመሪያ መተላለፉን ተናግረዋል።

በዚህም መንግስት የሰጣቸውን መመሪያና ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ግንባታቸውን ሳያጠናቅቁ ወደ ስራ በገቡ 19 አልሚዎችና ላይ የማሸግ ርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በክልሉ ለሚያለሙ ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ከማድረግ ጎን ለጎን መሬት ወስደው ወደ ስራ በማይገቡና ግንባታ ሳያጠናቅቁ አገልግሎት በሚሰጡ ባለሃብቶች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን ርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.