Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ከተማ ለባጃጆች የመለያ ባር ኮድ መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተሽከርካሪ በመታገዝ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለመከላከልና የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በባሕር ዳር ከተማ ለሚገኙ ባጃጆች(ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ) የመለያ ባር ኮድ የመስጠት መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ዘለቀ በዚህ ወቅት÷ በከተማው በተሽከርካሪ በመታገዝ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን ለመከላከል የመለያ ባር ኮዱን በየማህበራቱ የመለጠፍ ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ይህም ለትራንስፖርት መሳለጥ፣ለህዝብ ሰላምና ለአካባቢ ፀጥታ መጠበቅ እንዲሁም ለትራፊክ ደህንነት መረጋገጥና ሰላም የሰፈነበት የእንቅስቃሴ አውድ ለመፍጠር ትልቅ ድርሻ አለው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ከዚህ በኋላ በከተማው የሚገኝ ማንኛውም ባጃጅ ያለ ባር ኮድ መንቀሳቀስ እንደማይችል አውቆ የሚሰጠውን ባር ኮድ በመጠቀም በህጋዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንዳለበትም ነው ሃላፊው ያሳሰቡት፡፡

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው÷ ባር ኮዱ በከተማዋ በ18 ማህበራት ስር የሚገኙ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.