Fana: At a Speed of Life!

በካርቦን ሞኖክሳይድ መርዛማ ጋዝ 12 ሰዎች በተኙበት ሕይዎታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምሥራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ጆርጂያ በካርቦን ሞኖክሳይድ መርዛማ ጋዝ 12 ሰዎች በተኙበት ሪዞርት ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ክስተቱ ያጋጠመው በሀገሪቱ በሚገኝ ስኪ ሪዞርት መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ÷ 11 የውጭ ሀገር ዜጎች እና አንድ የጆርጂያ ዜግነት ያለው ሰው ሕይዎት ማለፉን እና 12 አስከሬን መገኘቱን ገልጿል፡፡

በሟቾች አስከሬን ላይ ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት አለመታየቱን ገልጾ÷ የአደጋው መንስዔ የካርቦን ሞኖክሳይድ መርዛማ ጋዝ ሳይሆን እንዳልቀረ ፖሊስ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

በሪዞርቱ በወቅቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ተከትሎ በነዳጅ የሚሠራ ጄኔሬተር አገልግሎት እየሠጠ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.