Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ላይ እየሰራች ላለው ስራ አድናቆት ተቸራት

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ገብሬላ ቻንግሰን ኢትዮጵያ በትምህርት ጥራት ላይ እየሰራች ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በደቡብ ሱዳን መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ዜጎች እየሰጠች ባለችው የትምህርት እድልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት ÷ሚኒስቴሩ ብቁ እና ክህሎት ያላቸውን ተማሪዎች ለማፍራት እየሰራቸው ስላለው ሪፎርሞች ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለደቡብ ሱዳን ዜጎች ባለፉት አመታት በርካታ የትምህርት እድል ሲሰጥ መቆየቱንም አንስተዋል።

የደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ገብሬላ ቻንግሰን በበኩላቸው÷የኢትዮጵያ መንግስት ለደቡብ ሱዳን ዜጎች በሰጠው የነጻ ትምህርት እድልና እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ላይ እየሰራች ስላለው ስራም ሚኒስትሩ ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.