የታንዛኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር መሃሙድ ታቢት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
መሃሙድ ታቢት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በሚጀመረው የኢትዮ- ታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው አዲስ አበባ የገቡት፡፡
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡