አቶ ጥላሁን ከበደ በወላይታ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው በወላይታ ሶዶ ከተማ እየለማ ያለውን የኮሪደር ልማት እና ከኮካቴ -ግብርና ኮሌጅ አስፓልት ሥራ ያለበትን ደረጃ እና ሌሎችንም የልማት ሥራዎች ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳደሩ በተጨማሪ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ የወላይታ ዞን የሥራ ሃላፊዎች እና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች መሳተፋቸውን የወላይታ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡