Fana: At a Speed of Life!

ለመስኖ ተጠቃሚነትና ስራ እድል ፈጠራ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመስኖ ተጠቃሚነት እና ስራ እድል ፈጠራ የተሰጠው ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው አስገነዘቡ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ሀላባ ዞን በቡና እና ፍራፍሬ ልማት ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደሮችን ማሣ በተመለከቱበት ወቅት÷ የአርሶ አደሩን የስራ ባህል በማሻሻል ሁሉንም ወራቶች ለልማት ስራ ማዋል ይገባል ብለዋል።

አዳዲስ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በዘርፉ የመስኖ ተጠቃሚነት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች ላይ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።

የግብርና ስራ ምንጊዜም የሚከናወን ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ የአርሶ አደሩ የስራ ባህል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳርፉ ጉዳዮች መቀረፍ እንዳለባቸውም መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.