የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች የዕውቅና መርሐ-ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች የዕውቅና መርሐ-ግብር በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው መርሐ-ግብሩ የተካሄደው፡፡
ዕውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊ የሆኑ 40 አርሶ አደሮች መሆናቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
አርሶ አደሮቹ በውድድሩ ላይ ቡናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጫርቶ በከፍተኛ ዋጋ ተሽጦላቸዋል ተብሏል፡፡