ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች ታገደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩክሬናዊው የቼልሲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሚካዬሎ ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች መታገዱ ተረጋግጧል፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ተጫዋቹ ያልተፈቀደ አበረታች ቅመም ተጠቅሟል በሚል ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡
ቼልሲ እና ተጫዋቹ ሙድሪክም የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር እያከናወነ ያለውን ምርመራ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል፡፡
የምርመራ ውጤቱ ይፋ እስከሚሆን ድረስም ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች መታገዱ ተነግሯል፡፡
ፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ በተመሳሳይ ኬዝ በፈረንጆቹ 2023 የአራት ዓመት ቅጣት ተላልፎበት እንደነበር እና በዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት አማካኝነት ወደ 18 ወራት ዝቅ እንዲልለት መደረጉ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም ቅጣቱን በማጠናቀቅ የፊታችን ጥር ወር ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡