አየር መንገዱ የቁልቢ ገብርኤል ተጓዦችን ለማጓጓዝ ዝግጅቱን አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓልን ለማክበር ወደ ቁልቢ ገብርኤል ለሚጓዙ መንገደኞች ተጨማሪ በረራዎችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ በረራዎቹ ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ያለምንም መንገደኛ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ማስተካከያ የሚደረግባቸው መሆናቸውንም ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው፡፡
የዋጋ ማስተካከያው ወደ ድሬዳዋ የሚደረጉ ሰባት ዕለታዊ መደበኛ በረራዎችን እንደማያካትትም ነው የተገለጸው፡፡
በዓሉን ተከትሎ ወደ ድሬዳዋ የሚጓዙ መንገደኞችን በተሳለጠ መልኩ ለማስተናገድ ለድሬዳዋ መንገደኞች ተለይቶ በተዘጋጀው የስልክ ቁጥር 6787 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻልም ተጠቁሟል።