Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት በአትሚስ እውቅና ተሰጠው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ለተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት የክብር ሜዳሊያ አበረከተ፡፡

 

ሰራዊቱ የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተለት በሶማሊያ ሰላም እና ጸጥታን ለማረጋገጥ በሰራው አስደናቂ ስራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 

የአትሚስ የጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ክንዱ ገዙ ÷ሰራዊቱ ላሳየው ቁርጠኝነት፣ሙያዊ ስነ-ምግባር  እና ለተልዕኮ አፈፃፀም አድናቆታቸውን ችረዋል፡፡

 

ሰራዊቱ ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት ለሰራው ስራ እንዲሁም  ለከፈለው መስዋዕትነት የክብር ሜዳሊያው መበርከቱንም  ነው ብርጋዴር ጄነራል ክንዱ የገለጹት፡፡

 

ኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ  ጀምሮ ለቀጣናው ብሎም ለአለም ሰላም መስፈን በከፍተኛ ቁርጠኝነት የድርሻዋን ስትወጣ መቆየቷን መናገራቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

በአትሚስ ውስጥ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ጄነራሉ ይህም ሀገሪቱ ለቀጣናው ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ቁርጠኛ መሆኗን አመላካች ነው ብለዋል፡፡

 

በአትሚስ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል በስፋት ፈንቴ÷ ሰራዊቱ በበርካታ ፈተናዎች በማለፍ ተልዕኮውን በብቃት መፈጸሙን ገልፀው የደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ግዛት አስተዳደርን  እና ማህበረሰቡን  በነበራቸው ቆይታ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

 

በእውቅና  መርሐግብሩ ላይ የአትሚስ መኮንኖች፣የአካባቢው ባለስልጣናት እንዲሁም  ሌሎች የፖለቲካ እና የማህበረሰብ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.