Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 154 የታጠቁ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 154 የታጠቁ ኃይሎች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለዋል።

በከለላ ወረዳ ሊጮ አካባቢ ተመሥርተው በአባ ጋስጫ፣ በሪማ፣ በጎረንጂ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ታጣቂዎች “የገባንበት የተሳሳተ መንገድ የሕዝባችንን ችግር የሚያባባስ እና የማያዋጣ መሆኑን በመረዳት መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለናል” ብለዋል።

ታጣቂዎቹ የኅብረተሰቡን ሰላም በማሳጣት ለከፋ ችግር ሲዳርጉ መቆየታቸውንም መናገራቸውን የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አሁን ላይ የተሰጣቸውን የሰላም አማራጭ በመጠቀም ሕዝብን ለመካስ እና ከመንግሥት ጎን በመሆን የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የቀረበላቸውን የሰላም ጥያቄ ተቀብለው ለሰላም የገቡ ታጣቂዎች በተደረገላቸው መልካም አቀባበልም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.