አየር መንገዱ “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ ስራ አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ አስጀመረ።
ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
ጥምረቱ የአየር መንገዱ ራዕይ 2035 አንዱ አካል ሲሆን÷ ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙ ይታወሳል።