በጎንደር ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትንና የሰላምን መረጋገጥ የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፉ መንግስት ሰላምን ለማስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመደገፍና የልማት ተግባራትን ለማገዝ ታሳቢ ያደረገ ነው።
በሰልፉ ‘ክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ልማት ነው፤ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን፤ የተጀመሩ ልማቶችን እናስቀጥላለን፤ ሰላም የጋራ ሃብት ነውና በጋራ እንጠብቀዋለን እና መንግስት ለከተማዋ ልማት እያደረገ ላለው ጥረት እናመሰግናለን’ የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ሰላምንና ልማትን የሚደግፈው ሰልፍ በከተማዋ ከሁሉም ክፍለ ከተሞችና ቀበሌዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን፥ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።
በሙሉጌታ ደሴ