በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሕር ዳር ከተማ “ሰላም ለሁሉም ፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሕዝባዊ ሰልፉ ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ልማት መሆኑን የሚያንጸባርቁ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ከተላለፉ መልዕክቶች መካከልም መንግሥት ሕግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል፣ ጽንፈኛው ሃይል በንጹሃን ላይ የሚፈጽመው ግድያ ሊቆም ይገባል፣ መከላከያ ሰራዊታችንና የክልላችን የጸጥታ ሃይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን የሚሉና ሌሎች ይገኙበታል፡፡
በደሳለኝ ቢራራ