Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ት/ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን እድሪስ እንዳሉት፥ በክልሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማሳለጥና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው።

አሁን ላይም ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል 11 ነጥብ 9 ሚሊየን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል።

በቅርቡ በክልሉ መንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካካል የተፈረመው የሰላም ሰምምነትም የትምህርት ሂደቱን ለማሳለጥ ሚናው ጉልህ መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ በጸጥታና ሌሎች ችግሮች 308 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ይማሩ የነበሩ አብዛኛዎቹ ተማሪዎቸ አቅራቢያ በሚገኝ ት/ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎም ትምህርት ቤቶችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ረገድም ከትምህርት ማህበረሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.