ከ330 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 331 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከሕዳር 27 እስከ ታሕሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትት ነው 308 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢና 23 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችን የያዘው፡፡
ከተያዙት እቃዎች መካከልም አልባሳት፣ኤሌክትሮኒክስ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ሐዋሳ፣ ሞያሌና ድሬድዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡