Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣናው ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስታውቋል፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከኢጋድ አባል ሀገራት የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራን እና የሚዲያ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም የሚስተዋሉ ዋልታ ረገጥ እሳቤዎችን መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ለቀጣናው የጋራ ልማት ከአጋር አካላትና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም የኢጋድ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በቀጣናው ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ  አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.