በአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ የተላለፉ መልዕክቶች
👉 በደምበጫ በገርጨጭ፣ በላሊበላና በሌሎች አካባቢዎች ንፁሃንን የጨፈጨፉ ፅንፈኛ ሀይሎች ለህግ ይቅረቡልን!
👉 ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን!
👉 መንግስት ህግ በማስከበር የንፁሃን ሰዎችን ገዳዮች ለህግ ያቅርብልን!
👉 መንግስት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን!
👉 ንፁሀንን በግፍ እየገደሉ በአስከሬናቸው መነገድ አረመኔያዊነት ነው!
👉 የልማት ማዕከል የነበረውን ክልላችንን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ የሚሠራው ሥራ የባንዳነትና የፅንፈኝነት ጥግ ነው!
👉 ለክልላችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላም እና ልማት ነው!
👉 ፅንፈኛ እና ተላላኪዎች ከባዕዳን ተልዕኮ ወጥተው የሰላምን አማራጭ ሊከተሉ ይገባል!
👉 ሰላም የጋራ ሀብት ነው፤ በጋራ ይለማል በጋራ ይጠበቃል!
👉 መንግስት ህግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል!
👉 ፅንፈኛው ሀይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል!
👉 መከላከያ ሰራዊታችን፣ የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች እና የክልላችን የፀጥታ ሀይሎ ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን!