ብሔራዊ ሙዝየም ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም ከጥገናና ሌሎች ሥራዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የተቋሙን ምድረ ግቢ ማስዋብን ጨምሮ የሙዝየሙን ሕንጻ የመጠገንና የዐውደ-ርዕይ የማሻሻያ ሥራዎች እየተሠሩ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የሙዚየም አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መቋረጡን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡