Fana: At a Speed of Life!

ፋብሪካው የታጠበ ከሰል ፍላጎትን 75 በመቶ ይሸፍናል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢት የከሰል ድንጋይ ማጠቢያና ማበልጸጊያ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የታጠበ ከሰል ፍላጎትን 75 በመቶ እንደሚሸፍን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ ፋብሪካውን በጎበኙበት ወቅት÷ ለከሰል ድንጋይ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማዳን የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ፋብሪካው በቅርቡ ተመርቆ በተሟላ መልኩ ወደ ሥራ ሲገባ ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አስረድተዋል፡፡

በኢት ማዕድን አክሲዮን ማኅበር በኩል ምርቱን በማጠብና በማበልጸግ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለማቅረብ የተጀመረው ተግባር አበረታች ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፋብሪካው በሠዓት 150 ቶን ጥሬ ከሰል እና በቀን 3 ሺህ 600 ቶን የታጠበ ከሰል የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.