Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የዳኝነትና የፍትሕ አካላት የምክክር መድረክ በአርባምንጭ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው ሀገር አቀፍ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረትና የፍትህ ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና አርዓያሥላሴን ጨምሮ ሌሎች የባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የፍርድ ቤቶች እና የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን የሶስት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በሕግ የበላይነት ዙሪያ ሠነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ መድረክ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዚን ፌሎውሽፕ ኢትዮጵያ ትብብር የተዘጋጀ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.