Fana: At a Speed of Life!

የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊዎች የተወካዮች ምርጫ እያከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሠ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኦሮሚያ ክልል የህብረተሰብ ክፍሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ እየተደረገ ነው።

በዛሬው ዕለት በቀጣይ የምክክር ሂደቶች የሚሳተፉ ተወካዮች ከአሥሩም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመረጡ ነው ሲሆን ፥ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ምርጫ በእያንዳንዱ የክላስተር ቡድን ደረጃ የሚከናወን ነው ተብሏል።

እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በክላስተር ደረጃ ሥምንት ተወካዮችንም በሚስጥራዊ መንገድ ይመርጣል እንደሀገራዊ ኮሚሽን መረጃ።

በአንድ ክላስተር 80 ተወካዮች ሲመረጡ፤ አንድ የህብረተሰብ ክፍል በክልል ደረጃ 32 ተወካዮች ይኖሩታል ፤ በኦሮሚያ ክልል አሥሩን የወረዳ የማህበረሰብ መሰረቶችን ወክለው አጀንዳ የሚያጠናቅሩ 320 ተወካዮች ይኖራሉ።

የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጉት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ደግሞ ከመጪው እሁድ ታህሣሥ 13/2017 ዓ/ም ጀምሮ ይከናወናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.