Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ሂዩስተን የሚገኘውን ቆንስላዋን እንድትዘጋ አሜሪካ አዘዘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ቴክሳስ ሂዩስተን የሚገኘውን ቆንስላዋን እንድትዘጋ አሜሪካ ትዕዛዝ ማስተላለፏ ተገለፀ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካ የአዕምሯዊ ንብረቶችን ለመጠበቅ ሲባል ነው ብሏል።

ቻይና የአሜሪካን እርምጃ የፖለቲካ ጠብአጫሪነት ስትል ገልፃዋለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ውሳኔውን አስደንጋጭ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ብለውታል።

አሜሪካ ቆንስላ ፅህፈት ቤቱ እንዲዘጋ ውሳኔ ያሳለፈችው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ቆንስላው በሚገኝበት አካባቢ ወረቀት ሲያቃጥል በተንቀሳቃሽ ምስል ከታየ በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ይህ እርምጃም ድሮም ቋፍ ላይ የነበረውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገ ተነግሯል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለይም ከንግድ እና ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ውጥረቶች እንደነበሩ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.