Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በወቅቱ ያልለማ 50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከባለሃብቶች እንዲነጠቅ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በወቅቱ ያልለማ 50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከባለሃብቶች ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የክልሉ ካቢኔ ውሳኔ አሳለፈ።

 

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

 

የከተማ ኢንቨስትመንትን ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እና መሬት ወስደው ወደሥራ ባልገቡ ባለሃብቶች  ርምጃ አወሳሰድ ዙሪያ የተወያየው ካቢኔው፤ በክልሉ በከተማ ኢንቨስትመንት ለመሠማራት ቦታ ወስደው በውሉ መሠረት በወቅቱ ያላለሙ ባለሃብቶች መኖራቸውን አይቷል።

 

በዚህም ቀደም ሲል ለባለሃብቶች ተሰጥቶ የነበረ እና በወቅቱ ያልለማ 50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከባለሃብቶች ተነጥቆ ወደመሬት ባንክ እንዲገባ እና ለአልሚ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ ውሳኔ አሳልፏል።

 

በተጨማሪም የከተማ ኢንቨስትመንት ቦታ የወሰዱ ከ80 በላይ ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ልማት እንዲገቡ ካቢኔው ማሳሰቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

 

እነዚህ ባለሃብቶች ላይ የቅርብ ክትትል ተደርጎ በወቅቱ ወደልማት የማይገቡ ከሆነ አስፈላጊው ርምጃ እንደሚወሰድም ተወስኗል።

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.