Fana: At a Speed of Life!

የጃፓኑ ኩባንያ በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ስራዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጃፓኑ ቶዮ ሶላር ኩባንያ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ለሚያከናውናቸው ስራዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ገለፀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ÷ከቶዮ ሶላር እህት ኩባንያ አባላንስ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሪዩ ጀንሴይ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷የኢትዮጵያን ሰፊ የኢንቨስትመንት አቅም እንዲሁም በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ስለሚገኙ የግብር እፎይታ፣ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጨምሮ ስለሚገኙ ጥቅሞች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ውስጥ በማኑፋክቸሪንግ፣ በንግድ፣ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ሰፊ አማራጮች ቀርበዋል ብለዋል።

ሪዩ ሪዩ ጀንሴይ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ መኖሩን ገልጸው ኩባንያቸው በኢትዮጵያ በተጨማሪ ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱን መናገራቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቶዮ ሶላር ኩባንያ መቀመጫውን ቬትናም ያደረገ የጃፓን ኩባንያ ሲሆን÷ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች አንዱ በሆነው የሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ በ60 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት በማድረግ ስራ የጀመረ ነው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.