Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በ423 ሚሊየን ብር ግድብና የመስኖ ፕሮጀክት ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል በጀረር ዞን ደገሀቡር ወረዳ በሚገኘው ጎሆዲ አከባቢ በ423 ሚሊየን ብር ግድብና የመስኖ ፕሮጀክት ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ለግድቡና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቱ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በሁለት ምዕራፍ የሚከናወነው የመስኖ ፕሮጀክቱ ህብረተሰቡንና እንስሳቶችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግና ለእርሻ ልማት ተጠቃሚነት እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በክልሉ የመስኖ እና የተፋሰስ ልማት ቢሮ አማካኝነት የሚካሄደው የመስኖ ፕሮጀክቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የታቀደ ሲሆን ፥ የመስኖ ፕሮጀክቱ 1ሺህ 300 ሄክታር መሬት ለማልማት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ የመስኖ ፕሮጀክት የአካባቢውን ህብረተሰብ ህይወት ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው ፥ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ በበኩላቸው ፥ የመስኖ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የእርሻ ልማት ስራዎችን በማሳደግ የህብረተሰቡን እንደሚለውጥ መግለጻቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.