Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመወያየት ባሕር ዳር ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ባሕር ዳር ገቡ፡፡

ባሕር ዳር ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን እና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ አደም በሚኖራቸው ቆይታ ከአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በሰላም፣ በልማት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.