ጀርመን የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴርን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘርፉ የምናደርገውን ጥረት ለመደገፍ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር አረጋግጠውልኛል ሲሉ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደርና የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ ታዛቢ አምባሳደር ጄንስ ሃኔፌልድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና የትብብር ሥራዎች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በውይይታቸውም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የክኅሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ዘርፍ ያለውን ሚና በተመለከተ መክረናል ነው ያሉት፡፡
የተመዘገቡ ውጤቶችም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤታማነት የሚያመላክቱ እና ለሰላምና መረጋጋት ብሎም ለቀጣናዊ ትስስር ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጀርመን በዘርፉ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደሩ አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡