Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እያሳደገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር በቀል የኢኮኖሚና ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እያሳደገ እንደሚገኝ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናገሩ።

የሀገር በቀል ኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለአምራች ዘርፉ ባመጣው እድል፣ ተግዳሮትና መፍትሄ ዙሪያ የግሉ ዘርፍና የመንግስት የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ መላኩ አለበል÷ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በርካታ ጠቀሜታዎችን ይዞ መምጣቱን አስረድተዋል።

ማሻሻያው የኢንዲስትሪ ሚኒስቴር ተግባራዊ እያደረገ ከሚገኘው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ውጤታማ የሆነ አምራች ዘርፍን መፍጠር እንደሚያስችል ጠቁመው÷ምቹ የቢዝነስ ከባቢን በመፍጠር ምርታማነትን እንደሚያሳድግም አስገንዝበዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መተግበር ተኪ ምርትን በማጠናከር የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ማስፋቱንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.