Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የሳይበር ጥቃት አደረሰች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በዩክሬን የመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ የተባለ የሳይበር ጥቃት መፈጸሟ ተሰሟ።

 

የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልሃ ስቴፋኒሺያ እንደገለጹት÷ በወሳኝ ኩነት መዝገብ ቤቶች ላይ በደረሰው በዚህ ጥቃት አገልግሎት ለጊዜው እንዲቋረጥ ተደርጓል።

 

በተመሳሳይ በዚህ ጥቃት ምክንያት በዩክሬን የፍትህ ሚኒስቴር ስር ያሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም ለጊዜው ሥራ ማቆማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

 

የጥቃቱ ኢላማ የሆኑት ተቋማት እንደ ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ እና የንብረት ባለቤትነት ያሉ ስለ ዩክሬን ዜጎች ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ ናቸው ተብሏል።

 

የጥቃቱ ዓላማ የዩክሬን የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ማደናቀፍ ነው ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

 

ስራዎችን ወደነበሩበት ለመመለስ ሁለት ሳምንታት እንደሚፈጅ ጠቁመው ነገር ግን ቢሮዎች አንዳንድ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል።

 

ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የዩክሬን እና የሩሲያ ተቋማት ከባድ የሳይበር ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.