Fana: At a Speed of Life!

ቴክኖ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ቁልፍ ሚና እያበረከተ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቴክኖ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ቁልፍ ሚና እያበረከተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቴክኖ “ኤ አይ” የተሰኘ አዲስ ቴክኖሎጂ ትናንት የተለያዩ የመንግስት አመራሮችና አጋር አካላት እንዲሁም የዘርፉ ባለሞያዎች በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡

ቴክኖጂው ሥራዎችን ከማቅለል ባለፈ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ድምጾችን ወደ ጽሑፍ መቀየርና ተያያዥ ሥራዎችን በቀላሉና በፍጥነት መከወን ያስችላል ተብሏል፡፡

ለዚህም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑ ነው የተመላተው፡፡

ቴክኖ በቅርቡ ቴክኖሊጂን በመታገዝ በኤ አይ የታገዙ ምርቶችን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.