በጋምቤላ ክልል ከጥቅምት ወር ጀምሮ የሠራተኞች ደመወዝ በአዲሱ ጭማሪ እንዲከፈል ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ከጥቅምት ወር ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በአዲሱ ጭማሪ እንዲከፈል ተወሰኗል።
የክልሉ መንግስት ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
በዚህም ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ሕግን ተከትሎ ተግባራዊ እንዲደረግ ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል።