Fana: At a Speed of Life!

ሐሰተኛ የማንነት ማስረጃ አዘጋጅ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ሐሰተኛ ማስረጃ እያዘጋጀ ለሰዎች ሲሰጥ ነበር የተባለ ግለሰብ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ወደ ኤጀንሲው አገልግሎት ለማግኘት የመጣች ተገልጋይ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ጥቆማውን ተከትሎ በተካሄደ ኦፕሬሽን በ20 ሺህ ብር መታወቂያና የልደት ምሥክር ወረቅት ለማዘጋጀት ተስማምቶ ከግለሰቧ ፎቶና ሌሎች መረጃዎችን ጨምሮ ቀብድ 10 ሺህ ብር ሲቀበል በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.