Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የተገኘው ሰላም መንግስትና ሕዝብ ፊታቸውን ወደ ልማት እንዲያዞሩ አስችሏል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተገኘው ሰላም የልማት ሥራዎችን ማፋጠን የሚያስችል መሆኑን በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በፌዴራልና በክልሉ አመራር አባላት ተጎብኝተዋል።

በወቅቱ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት÷ የኮሪደር ልማቱ የከተሞችን እድገት የሚያፋጥን፣ ገጽታቸውን የሚቀይርና የሕዝቡን ኑሮ የሚያሻሽል ነው።

በዚህም በፓርቲ ደረጃ ታምኖበት በአዲስ አበባ ሥራውን በማስጀመር በኢትዮጵያ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች በማስፋት የከተሞችን ደረጃ በማሻሻል ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአማራ ክልልም የሰፈነውን ሰላም በመጠቀም የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች እየተፋጠኑ እንደሚገኙ ባደረጉት ጉብኝት ማረጋገጥ እንደቻሉ ተናግረዋል።

በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሁሉንም መሰረተ ልማቶች በማቀናጀት እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን ጠቁመው÷ ይህም የአገልግሎት ጥራት የሚያሳድግ፣ የጊዜና የሃብት ብክነትን መቀነስ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ የእግረኛ፣ የሳይክል፣ የአስፋልት መንገዶች፣ የአረንጓዴ ቦታዎች፣ የመዝናኛ እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎችን አካትቶ እየተገነባ በመሆኑ ከተማዋን የሚያዘምን እንደሆነ ነው የገለጹት።

ለዚህም የኤሌክትሪክ ሀይል፣ የውሃ፣ የቴሌ፣ የፍሳሽና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጡ ተቋማት ተቀናጅተው እየገነቡ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለመጪው ትውልድ ጭምር ታልሞ በጥራት እየተከናወነ መሆኑን መገንዘባቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት የስርዓተ ምግብን በማሻሻል፣የስራ እድል በመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካትና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት አስተዋጽኦው የጎላ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.