Fana: At a Speed of Life!

በሞዛቢክ ዝናብ በቀላቀለ አውሎ ነፋስ 73 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜናዊ ሞዛቢክ ሳይክሎን ችዶ በተባለ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ የተፈጥሮ አደጋ 73 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ለሁለት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን መታወጁ ተገልጿል።

በአደጋው በሰሜናዊ ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ፣ ናምፑላ እና ኒያሳ በተባሉ ግዛቶች በአጠቃላይ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ብሔራዊ ተቋም እንዳስታወቀው፤ በአደጋው 36 ሺህ 207 መኖሪያ ቤቶች፣ 48 ሆስፒታሎች፣ 186 የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ 9 ውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች እና 171 ጀልባዎች ወድመዋል፡፡

በተጨማሪም 149 ትምህርት ቤቶች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በዚህም ከ15 ሺህ በላይ ተማሪዎች እና 224 አስተማሪዎች ከመማር ማስተማር ስራ መራቃቸው ተመላክቷል፡፡

የተከሰተው ሳይክሎን ችዶ በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር እንደሚያካልል የተገለፀ ሲሆን በቀን ብቻ እስከ 250 ሚሊ ሜትር ልኬት ያለውን ዝናብ መቀላሉ ነው የተለፀው፡፡

ሳይክሎን ችዶ በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ ከተከሰቱ እና ብዙ ውድመት ካስከተሉ ውሽንፈሮች በአራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ጉዳት የደረሰባቸውን መልሶ የማቋቋም ስራ እንዲሁም ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሞዛምቢክ በፈረንጆቹ 2019 ሳይክሎን ኢዳይ በተባለው ውሽንፍር ክፉኛ ተመትታ በአደጋው 602 ሰዎች ሲሞቱ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ኢስት አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.