Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያና የፀጥታ ሃላፊዎች መደበኛ ስብሰባ በኪጋሊ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ክልላዊ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን “የሁለት አስርት ዓመታት ቁርጠኝነት” በሚል መሪ ሃሳብ 33ኛው የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያና የፀጥታ ሃላፊዎች መደበኛ ስብሰባ በርዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ በቀጣናው ውስጥ መረጋጋትን እና ደህንነትን ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

በመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በውይይቱ እየተካፈለ ይገኛል።

በውይይቱ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማጠናከር በቁልፍ የደህንነት ጉዳዮች እና ለቀጣይ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ማየትና በቀጣናው ባለው ወቅታዊና ወሳኝ የደህንነት ችግሮች ላይ መፍትሄና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ፍኖተ ካርታ ይዘረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል በክልሉ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና በአባል ሀገራት መካከል ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ትብብርን ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየት መቀጠሉን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.