የኢትዮጵያ ልዑክ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚያስችል ጉብኝት በኬንያ አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ጉብኝት በኬንያ አካሄደ።
ልዑኩ ከኬንያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝቶ ውይይት ማድረጉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
ጌዲዮን (ዶ/ር) ከኬንያ ካቢኔ፣ የዳያስፖራና ውጭ ጉዳይ ተቀዳሚ ሚኒስትሩ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ከሀገሪቱ የኢነርጂና ነዳጅ ሚኒስትር ኦፒዮ ዋንዳዪ ጋር ልዑኩ በነበረው ውይይት፤ በታዳሽና ዘላቂ ኢነርጂ መስክ ያለውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር ማድረጉ ተገልጿል።