Fana: At a Speed of Life!

ከ443 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ443 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ከታሕሣሥ 4 እስከ ታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 422 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ገቢ እና 20 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡

ከተያዙት እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒትና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ሞያሌ እና አዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.