Fana: At a Speed of Life!

የታጠቁ ሃይሎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታጠቁ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም እንዲመጡ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነትና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ የመጀመሪያው የሃይማኖቶች የሰላም ጉባዔ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ ፣የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተወካይ አቡነ ፊሊጶስ÷ የትላንት አባቶች የሰላም፣ የመተባበርና የአንድነት ምሳሌ ነበሩ፤ የአሁኑ ትውልድ ይሄንን ተቀብሎ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው÷በሃሳብ ልዩነት ውስጥ ያሉ አካላት በንግግርና በድርድር ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በቅርቡ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም የመጡ የኦነግ ታጣቂዎችንም አመስግነዋል፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.