Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር በላይ ሰብል ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በ2016/17 መኸር ምርት እስካሁን ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር በላይ ሰብል መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ በምርት ዘመኑ 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀሪ ቀናት በዘር የተሸፈነ ሰብል ሙሉ በሙሉ በመሠብሠብ አርሶ አደሩ መስኖ ልማት ላይ እንዲረባረብ እየተሠራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ቀሪ ያልተሠበሠበ ሰብል መሠብሠብ፣ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንዲጠናቀቁ ቢሮው አሳስቧል፡፡

የግብርና ባለሙያዎችም ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.