የሀውቲ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ያስወነጨፉት ሚሳኤል ኢላማውን እንደመታ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ያስወነጨፉት ባለስቲክ ሚሳኤል ወታደራዊ ኢላማውን እንደመታ አስታወቁ።
የእስራኤል ጦር ከሀውቲ ታጣቂዎች የተተኮሰውን ሚሳኤል ጠልፎ መጣል ወይም ማክሸፍ ሳይችል ቀርቶ በቴል አቪቭ አጠገብ ጃፋ ላይ መውደቁን ገልጿል።
ከየመን የተወነጨፈው የሀውቲ ባለስቲክ ሚሳኤል በማዕከላዊ እስራኤል አካባቢ ሲወድቅ በትንሹ 16 ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት አረጋግጧል።
የየመን ሁውቲ ቃል አቀባይ በቴል አቪቭ አጠገብ ጃፋ አካባቢ ወታደራዊ ኢላማችንን በባለስቲክ ሚሳኤል መትተናል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።