Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንጻ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ22 ሚሊየን ዶላር ወጪ ለበረራ ባለሙያዎች የተገነባውን ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንጻ አስመርቋል፡፡

በ1 ዓመት ከአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ለምረቃ የበቃው የመኪና ማቆሚያው በ48 ሺህ ስኩዌር ካሬሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ህንጻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ1 ሺህ 300 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችለው ማዕከሉ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነና በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመለት ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ድንገተኛ የእሳት አደጋን መቋቋም እንዲያስችል ተደርጎ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ የተገነባ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት በ2ኛ ዙር የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለ5 ሺህ ሰራተኞቹ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑንም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.