ማንቼስተር ሲቲ ዛሬም ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስቶንቪላ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በቪላ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ የነገሡት አስቶንቪላዎች÷ ጆን ዱራን በ16ኛው እንዲሁም ሞርጋን ሮጀርስ በ65ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተጋጣሚያቸውን ረትተዋል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ጎል ደግሞ ፊል ፎደን በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
እንደአጀማመራቸው መሆን እየተሳናቸው ያሉት ውኃሰማያውዮቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስኬታማ መንገድ ላይ እንዳልሆኑ እየተመለከትን ነው፡፡
የዛሬውን ውጤት ተከትሎም አስቶንቪላ በ28 ነጥብ 5ኛ ላይ ሲቀመጥ÷ ማንቼስተር ሲቲ በአንድ ነጥብ ተበልጦ ወደ 6ኛ ደረጃ ዝቅ ለማለት ተገድዷል፡፡
የዛሬው የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥል በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ ከብራይተን፣ ኢፕስዊች ታውን ከኒውካስል ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ይገናኛሉ፡፡
እንዲሁም 2 ሠዓት ከ30 ላይ ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል ይፋለማሉ፡፡