የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የገጠሩን የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ አድርጓል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል እየተተገበረ ያለው የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የገጠሩን የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ የ2017 ዓ.ም የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በአማራ ክልል እየተተገበረ ያለው የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን በተለይም የገጠሩን የሕብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ እያደረገ ነው።
የጤና ፋይናንስ ተዘርግቶ እንደ አንድ የትኩረት መስክ በትኩረት እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የጤና መድኅን ሥራዎችን በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡