Fana: At a Speed of Life!

በንጹህ መጠጥ ውኃ ተቋማት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተፈጥሮ አደጋ በንጹህ መጠጥ ውኃ ተቋማት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

በደቡብ ጎንደር ዞን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ወረዳዎች የተጎዱ የመጠጥ ውኃ ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር 7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 62 ፓምፖችን ድጋፍ ማድረጋቸውን የቢሮው ኃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ቢሮው ነዋሪዎች በውኃ ወለድ በሽታ እንዳይጠቁ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ÷ የንጹህ መጠጥ ውኃ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች በስኬት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.