አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 33 አሳደገ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው አርሰናልን ያስተናገደው ክሪስታል ፓላስ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
የመድፈኞቹን ጎሎችን በ6ኛው እና 14ኛው ጄሱስ፣ በ38ኛው ሀቨርትዝ፣ በ60ኛው ማርቲኔሊ እንዲሁም በ84ኛው ደቂቃ ራይስ አስቆጥረዋል፡፡
ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን ወደ 33 በማሳደግ በደረጃ ሠንጠረዡ ሦስተኛ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡
16 ነጥቦችን ይዞ 15ኛ ደረጃ ለሚገኘው ክሪስታል ፓላስ ደግሞ ሳር በ11ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ዌስትሃም ከብራይተን ጋር አንድ አቻ ሲለያዩ÷ ኢፕስዊች ታውን በኒውካስል ዩናይትድ 4 ለ 0 እንዲሁም ብሬንትፎርድ በኖቲንግሃም ፎረስት 2 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡
በሌላ በኩል 9 ከ30 ላይ በተደረገ ጨዋታ በሜዳው ማንቼስተር ሲቲን ያስተናገደው አስቶንቪላ 2 ለ 1 ረትቷል፡፡