ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን አቻው ጋር የቻን ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር (ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 11 ሰዓት በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።
ጨዋታውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ሊቢያ ያቀና ሲሆን ለሁለት ቀናት በቤንጋዚ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።